Fana: At a Speed of Life!

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝቡን የሰላም ጥያቄዎች ለመመለስ በተከናወነ ሥራ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

በምዕራብ ኦሞ ዞን ‘ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ተግባራዊ ሚና፤ ከግጭትና ሞት አዙሪት ወደ ሁለንተናዊ ልማት’ በሚል መሪ ሐሳብ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ እስካሁን የተሠሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ብሎም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ በሕዝቡ የሚነሱ የሰላም፣ ልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

በተለይም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የሰላም መደፍረስ ችግር ለመፍታት በየደረጃው ያለውን የፀጥታ መዋቅር ከሕዝቡ ጋር በማቀናጀት ሰፊ ሥራ በመከናወኑና ሰላም በመስፈኑ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውም ጨምሯል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በክልሉ በተሠሩ ሥራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ አሁንም በምዕራብ ኦሞ ዞን ዘላቂ ሰላም በማስፈን ሕዝቡን በልማት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በዚህም ውስጣዊ እና ውጫዊ ግጭቶች እንዲሁም ዝርፊያዎች እንዲፈቱ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.