“የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው የንግድ ትርኢት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 14ኛው “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ተሰናድቶ የቆየው የንግድ ትርኢት ተጠናቅቋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የንግድ ትርኢቱ ሸማች እና አምራችን በቀጥታ ከማገናኘቱም ባሻገር የሀገራችንን እምቅ አቅም ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነበር ብለዋል፡፡
በመድረኩ በመሳተፍ እና በማስተባበር አበርክቶ ለነበራቸው አካላት ምስጋናና እውቅና እንደተበረተላቸውም ተጠቁሟል፡፡
የንግድ ትርዒቱ ከመጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።