Fana: At a Speed of Life!

ለበልግ እርሻ 500 ሺህ ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር መዘጋጀቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለዘንድሮው የበልግ እርሻ 500 ሺህ ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር መዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የግብርና ግብዓት ሥነ-ሕይወታዊ ዘርፍ ሃላፊ ስመኝ ተጫነ ÷ ለበልግ እርሻ ግማሽ ሚሊየን ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ተዘጋጅቶ ክልሎች በፍጥነት ለአርሶ አደሩ እንዲያሰራጩ አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረዋል፡

አርሶ አደሮች በስፋት የሊሙ እና ሾኔ በቆሎ ምርጥ ዘሮችን መጠቀም እንዳለባቸውም ሃላፊው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡

በሌላ ኩል አርሶ አደሮች የተሻለ ምርት የሚሰጡ ሀገር በቀል የበቆሎ ምርጥ ዘሮችን እንዲጠቀሙ የግንዛቤ  መፍጠር ሥራ ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የበቆሎ ምርጥ ዘርን ፍላጎት በሀገር ውስጥ አቅም ለመሸፈን በተሰራው ሥራ ለዘንድሮ ዓመት የበቆሎ ምርጥ ዘር ከውጪ አለመግባቱን አመላክተዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.