ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የተፈጥሮ ጥበቃ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተፈጥሮ ጥበቃ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ ልዩ ወረዳ፣ ቃሉ፣ ደሴ ዙሪያ እና ለጋምቦ ወረዳዎች ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተግባር ከችግኝ ማፍላት ጀምሮ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አጋርተዋል፡፡
መሬትን መንከባከብ ስንችል፤ ልዩ ስጦታ የሆነውን የመኖር ዋስትና እንዲሁም በምግብ ራስን የመቻል ነፃነት እናገኛለን ነው ብለዋል።
በዚህ ተግባር ላይ እተሳተፉ ያሉ አካላትን አመሥግነው፤ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡