116ኛው የፖሊስ ቀን ሚያዝያ 26 ይከበራል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 116ኛው የፖሊስ ቀን “ለተለወጠ ሀገር ያደገ ፖሊስ” በሚል መሪ ሐሳብ የተለያዩ ዝግጅቶች ሚያዝያ 26 ይከበራል።
ቀኑን በማስመልከት የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ ተቋማት የሚሳተፉበት 5ኛው የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ስፖርት ውድድር በአበበ ቢቂላ ከሚያዝያ 19 እስከ 25 ቀን 2017 እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ከሚያዝያ 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲምፖዚያም እና አውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዚየም እንደሚካሄድም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።
116ኛው የፖሊስ ቀን ማጠቃለያ መርሐ ግብር ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በደማቅ ወታደራዊ ትርዒት እንደሚከናወንም ተገልጿል።
ኅብረተሰቡ በፕሮግራሞቹ ላይ በመገኘት ለፖሊስ ያለውን ድጋፍ እንዲያሳይም ጥሪ ቀርቧል።