Fana: At a Speed of Life!

ለፓስፖርት አገልግሎት የፋይዳ መታወቂያ ቅድመ ሁኔታ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለፓስፖርት አገልግሎቶች የፋይዳ መታወቂያን እንደ ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ከብሀየራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ደረሱ።

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት የጀመራቸውን የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ቅድመ ሁኔታ ለማድረግ እየሰራ መቆየቱን ገልጿል፡፡

አገልግሎቱ ለፓስፖርት አሰጣጥ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ በማድረግ በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ደህንነታቸውን የጠበቁና ተደራሽ ለማድረግ ከዲጅታል መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምቷል።

ይህም ማንነትን በማጭበርበር የተለያዩ ሰነዶችን ለማግኘት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመግታት እንደሚያስችል ተገልጿል።

በመሆኑም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ በቅድሚያ በፋይዳ ተመዝግበው ልዩ ቁጥር ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመላክቷል።

ተገልጋዮች የፋይዳ መታወቂያቸውን በወረቀት መልክ አሳትመው እንዲሁም ዲጂታል ኮፒውን በስልካቸው ይዘው በመምጣት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.