Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት አኅጉራዊ ጉባዔን ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከግንቦት 11 እስከ 15 ቀን 2017 ድረስ 20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት አኅጉራዊ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ ጉባዔውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ በየሁለት ዓመቱ የሚዘጋጀው ይህ ጉባዔ ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በጉባዔው ላይም ከ50 ሀገራት የተውጣጡ 1 ሺህ 500 ተሳታፊዎች እንደሚጠበቁ ገልጸዋል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.