ካሳሁን ዘውዱ የፋና ላምሮት የምዕራፍ 19 የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ካሳሁን ዘውዱ የፋና ላምሮት የምዕራፍ 19 የፍጻሜ ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡
ለሶስት ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው ፋና ላምሮት የምዕራፍ 19 የፍጻሜ ውድድር ዛሬ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
ለፍጻሜ ውድድሩ አራቱ ተወዳዳሪዎች ማለትም ብሩክ ሰለሞን፣ ዮሴፍ ጉልላት፣ ካሳሁን ዘውዱ እና ኤፍሬም ጌታቸው ብርቱ ፉክክር አድርገዋል፡፡
ተወዳዳሪዎቹ በሶስት ዙር የመረጧቸውን ሙዚቃዎች ከኮከብ ባንድ ጋር ያቀረቡ ሲሆን÷ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተወዳዳሪዎቹ የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡
በዚህም ካሳሁን ዘውዱ የፋና ላምሮት የምዕራፍ 19 የፍጻሜ ውድድሩን በማሸነፍ የ400 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በተመሳሳይ ኤፍሬም ጌታቸው በፍጻሜ ውድድሩ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የ300 ሺህ ብር ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡
እንዲሁም ብሩክ ሰለሞን 3ኛ እና ዮሴፍ ጉልላት 4ኛ ደረጃን በመያዝ በቅደም ተከተል የ200 ሺህ ብር እና የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ