Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ላይ የሜዳ እና የሰዓት ለውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀዋሳ ከተማ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀሪ 4 ጨዋታዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳ እና የሰዓት ለውጥ መደረጉን የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አሳወቀ።

ጨዋታዎቹን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለማካሄድ መርሐ ግብር የወጣ ቢሆንም እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሰዓት እና የቦታ ለውጥ ተደርጎ ሎጊታ በሚገኘው በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

ዛሬ ቀን 9 ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሊደረግ የነበረው የወላይታ ድቻ እና አርባ ምንጭ ከተማ ጨዋታ የቦታ ለውጥ ተደርጎበት በተመሳሳይ ሰዓት ላይ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ይደረጋል፡፡

ሌላኛው የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ የሆነው የኢትዮጵያ መድን እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ መቼ እንደሚደረግ ወደ ፊት እንደሚያሳውቅ የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴው አሳውቋል፡፡

በተመሳሳይ ነገ የሚደረጉ የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ የሰዓት እና የቦታ ለውጥ የተደረገ ሲሆን÷ ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ቀን 7 ሰዓት እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከመቻል 10 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

ሊጉን ኢትዮጵያ መድን በ54 ነጥብ ሲመራው÷ ኢትዮጵያ ቡና በ45 እንዲሁም ባህርዳር ከተማ በ43 ነጥብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.