Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን በይበልጥ ማሳደግ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ዘርፍን ለማነቃቃት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች በመሆናቸው በይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ምሁራን ተናገሩ፡፡

የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ለጋራ ትርክት ግንባታ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው ዘርፉን በይበልጥ ለማልማት መትጋት እንደሚገባ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም መምህር የሆኑት ዓለማየሁ አካሉ (ዶ/ር) መክረዋል፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም መምህሩ አሥራት ደስታ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር ያለውን ድንቅ ተፈጥሮ፣ ታሪክና ባህል በአግባቡ በማልማት የጋራ ትርክት እና ብሔራዊ ገፅታን ለማስረፅ እንዲያግዝ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በየአካባቢው ያሉ መስኅቦችን ለይቶ ለጎብኚዎች በማስተዋወቅ ረገድ በይበልጥ መሥራት እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላትም የድርሻቸውን እንዲወጡ ምሁራኑ ጠይቀዋል፡፡

በኢብራሂም ባዲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.