Fana: At a Speed of Life!

ከ600 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የመኸር ወቅት የሚውል 684 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መግባቱን በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር አስታወቁ፡፡

1 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት መታቀዱን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

እስከ አሁን ወደ ክልሉ ከገባው መካከልም ከ560 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየተሠራጨ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የምርጥ ዘር አቅርቦት እና ሥርጭት እጥረት እንዳይኖር የተለያዩ አማራጮች መዘርጋታቸውንም አሳውቀዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.