Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብጹአን አባቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዛሬው ዕለት ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን ከጎበኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብጹአን አባቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት ቤተ እምነቶቻችን የሀገር ህልውና መሰረት፣ የባህልና የታሪክ ምልክት፣ የማንነት ውቅር ካስማዎች ናቸው ብለዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት በሀገሪቱ የሰላም ግንባታ፣ በልማትና በማህበራዊ ትስስር የዜጎችን የሥነ ምግባር እሴቶች በማጎልበት ረገድ የሚያከናውኗቸውን በጎ ተግባራትና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ መደገፍ የመንግሥት ሀላፊነትና ግዴታ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.