Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በባሕር ዳር ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

ፓርቲዎቹ  ውይይት እያደረጉ ያሉት፤ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተግባር እና ኃላፊነትን በተመለከተ እንዲሁም በዴሞክራሲያዊ ዕድገት ዙሪያ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተከሰተው ቀውስ የሀገሪቱን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታውን አናግቶታል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የነበረውን ቀውስ መጋፈጥ በመቻላችን እና ስለ እውነት በመታገላችን አንጻራዊ ሰላም ውስጥ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ሕዝብ እረፍት እንዲያገኝ፤ በሰላም አየር ውስጥ እንዲንቀሳቀስ እና አሁን ያለው አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ገዥው ፓርቲም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አሁን ካለው የሰላም ሁኔታ አንፃር ትልቅ ተግባር ይጠበቅብናል በማለት “ስለ ሀገራችን መፃዒ እጣ ፈንታ መምከር አለብን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.