Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ302 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛና 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይወስዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል 302 ሺህ 516 ተማሪዎች የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይወስዳሉ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ የ2017 ዓ.ም ክልላዊ ፈተናዎችን በስኬት ለማጠናቀቅ አስፈላጊ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።

በክልሉ ሰኔ 3 እና 4 የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እንደሚሰጥ ገልጸው÷ ፈተናው በ2 ሺህ 642 ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥና 148 ሺህ 256 ተማሪዎች እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ሰኔ 5 እና 6 የስድስተኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ የገለጹት ኃላፊው÷ በፈተናው 154 ሺህ 260 ተማሪዎች በ3 ሺህ 551 ትምህርት ቤቶች ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል።

በሁለቱም የትምህርት ደረጃዎች ለቀናት በሚሰጠው ክልል አቀፍ ፈተና 302 ሺህ 516 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉም ነው ያሉት።

ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ወደ ፈተና ጣቢያዎቹ መድረሱን ጠቁመው÷ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ በክልል ደረጃ የፈተና ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.