Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ የለውጥ ሞተር በመሆን የመንግሥት ሠራተኛው ሚና ጉልህ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ለውጥ ላይ ናት፤ የለውጡ ሞተር በመሆን ደግሞ የመንግሥት ሠራተኛው ሚና ጉልህ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

“ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ የመንግሥት ሠራተኞች የማጠቃለያ ውይይት ተካሒዷል።

በውይይቱም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አንሥተዋል።

የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የነበሩ ችግሮችን ማስተካከል እየተቻለ መሆኑን ገልጸው፤ ከህዝቡ ገንቢ አስተያየቶች እየመጣ ነው ሲሉ አክለዋል።

በተወሰነ መልኩ የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያጠለሹ መኖራቸውን አንሥተው፤ ይህንን ለማሥተካከልም ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።

በለውጥ ሥራው የሠራተኛው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተነቃቅቶ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ልዩ ልዩ የማትጊያ ሥርዓቶች ተዘርግተዋል ነው ያሉት።

የኑሮ ጫናን ለመቋቋም በርካታ ድጋፎችን እየተደረጉ መሆኑን በማንሳት፤ የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት እንዲሁም የደመወዝ ጭማሪ ከማትጊያዎቹ መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሲቪል ሰርቫንቱ በመርህ ላይ ተመሥርቶ የሚሠራ እንዲሆን ለማስቻል የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል ነው ያሉት።

ሠራተኛውን የጥቅም እና ሌሎች መብቶቹን ለማሥከበርም እየሠራ ነው ብለዋል።

በሰለሞን ይታየው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.