Fana: At a Speed of Life!

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ባለሙያዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን እየጎበኙ ነው።

‎ባለሙያዎቹ በጉራጌ ዞን የግቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ጨምሮ በዞኑ የሚገኙ ባህላዊ መስህቦችን ተመልክተዋል።

‎የግቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ በክልሉ የሚገኝ ብቸኛ ፓርክ ሲሆን÷ ‎በውስጡ የያዛቸው መልከዓ ምድራዊ እና ተፈጥሯዊ መስህቦች በቱሪስቶች ተመራጭ ያደርገዋል።

‎ይሁን እንጂ ፓርኩ እና መሰል መስህቦች መዳረሻ የመሆን አቅማቸው ከፍተኛ ቢሆንም የማስተዋወቅ ስራ ባለመሰራቱ ተገቢውን ጎብኚ ቁጥር እያስተናገዱ አለመሆናቸው ተገልጿል።

እንዲሁም በቀቤና ልዩ ወረዳ የቀቤና ባህል ማዕከልን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎቹ ጎብኝተዋል።

‎በቱሪዝም ሚኒስቴር የተመራው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ቡድን ጉብኝት መስህቦቹን ለማስተዋወቅ ያለመ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው የመስህብ ስፍራዎች ጉብኝት ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

‎በሚኪያስ ዓለሙ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.