Fana: At a Speed of Life!

ከ40 ቢሊየን ብር በላይ የጡረታ መዋጮ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት ከ40 ቢሊየን ብር በላይ የጡረታ መዋጮ ሰበሰበ፡፡

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ድሬዳዋ ዲስትሪክት ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል፡፡

የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባተ ምትኩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ አሁን ላይ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የግል ድርጅት ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስትና አግልገሎት ምዝገባ አድርገዋል፡፡

ከ280 ሺህ በላይ የግል ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን በማስመዝገብ ከ2004 ጀምሮ ከ161 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸው÷ በዚህ ዓመት ብቻ ከ40 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አመልክተዋል።

ለጡረታ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለኢንቨስትመንት በማዋል ከ38 ቢሊየን ብር ማትረፉን እና አሁን ላይ ከ63 ሺህ በላይ የግል ድርጅት ሠራተኞች የማህበራዊ ዋስት ጡረታ አበል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሐርቢ ቡኽ በበኩላቸው÷ የጡረታ አቅድ ሽፋንን የማዘመንና ተደራሽ የማድረግ ስራ ለድህነት ቅነሳና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

አስተዳደሩ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያው በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እያበረከተ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.