ከአሰቃቂው የአውሮፕላን አደጋ የተረፈችው ነፍስ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቪሽቫሽ ኩማር ራሜሽ ትውልደ ህንዳዊና የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ግለሰብ ነው።
ግለሰቡ ቀደም ብሎ ከእንግሊዝ ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ ህንድ ያቀና ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት በህንድ ከተከሰተው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ መትረፉ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ቪሽቫሽ ኩማር ራሜሽ ከህንድ ወደ ለንደን እየተመለሰ በነበረበት ወቅት በተሳፈረበትና ቦይንግ 787-8 የሚል ስያሜ ባለው አውሮፕላን አሰቃቂ አደጋ ተከስቷል።
ይሁን እንጂ ቪሽቫሽ በአውሮፕላኑ መስኮት በኩል መቀመጡ ከአደጋው ህይወቱ እንዲተርፍ ምክንያት መሆኑን ተናግሯል፡፡
ግለሰቡ ከአሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላኑ ከተነሳ 30 ሴኮንድ በኋላ ከፍተኛ ድምፅ ማሰማት መጀመሩን እና ወዲያው በሴኮንዶች ልዩነት መከስከሱን ለሂንዱስታን ታይምስ ገልጿል፡፡
ከአውሮፕላኑ መከስከስ በኋላ ራሴን ስቼ ነበር፤ ነገር ግን ስነቃ የሞቱ ሰዎች አስከሬን አጠገቤ ነበር፤ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን ሳይ ተነስቼ ሮጥኩኝ ሲልም አክሏል፡፡
በአደጋው ሰውነቱ ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው ግለሰቡ÷ ሰዎች ደርሰው ወዲያ ወደ ሆስፒታል እንደወሰዱት እና ህክመናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡
ግለሰቡ በእግሩ፣ በደረቱ እና በዓይኖቹ ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት የኤ ኤን አይ ዘገባ አመላክቷል፡፡
በህንድ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን የ204 ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን÷ ቀሪ ሰዎችን የመፈለግ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!