በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተገነባው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ነገ ይመረቃል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተገነባው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሬዲዮ ነገ ይመረቃል አሉ።
አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የማህበረሰብ ሬዲዮው የተገነባው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴውን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ነው።
ዩኒቨርሲቲው ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት የማህበረሰብ ሬዲዮ ግንባታው መከናወኑን ገልጸው፤ ግንባታው በሚፈለገው ጥራት ከተያዘለት ጊዜ አስቀድሞ መጠናቀቁን ጠቁመዋል።
ለዚህም ከዩኒቨርሲቲው ጋር የቆየ ወዳጅነት ላለው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ምስጋና አቅርበው፤ በቀጣይ ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የማህበረሰብ ሬዲዮው የዩኒቨርሲቲውን ሁለንተናዊ ተግባር ከማስተዋወቅ ባለፈ ለጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል አማራጭ የተግባር ልምምድ ማዕከል በመሆን ያገለግላል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው በነገው ዕለት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተገነባውን የማህበረሰብ ሬዲዮ ጨምሮ 22 ፕሮጀክቶችን ያስመርቃል።
በምናለ አየነው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!