አዋጁ ከዓለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ ነው – የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የተሻሻለው አዋጅ ሽብርተኝነትንና ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ ነው አለ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት።
በወንጀል ድርጊት የተገኘን ንብረት ወይም ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005ን ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1387/2017 ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል።
በተሻሻለው አዋጅ ዙሪያ ለሕብረተሰቡ ተጨማሪ መረጃን ተደራሽ ለማድረግ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1387/2017 ከነባር አዋጁ 780/2005 በ58 አንቀጾች 14ቱ ላይ ማሻሻያ አድርጓል ብለዋል።
አዋጁ ሽብርተኝነትንና ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል።
የማሻሻያ አዋጁ በወንጀል ተግባር የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል ድርጊትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ላይ ኢትዮጵያ ድርሻዋን በአግባቡ እንድትወጣ ያስችላል ብለዋል።
አዋጁ አመንጪ የሚባሉ 21 ወንጀሎችን በአባሪነት ያስቀመጠ ብሎም ለትርጉም ተጋላጭ የነበሩ ጉዳዮችን በግልጽ የሚየስቀምጥ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ተገቢ ምርመራ ለማካሄድ ይጠቅማል ነው ያሉት።
በወንጀል ድርጊት የቅጣት አለመመጣጠን መልክ ማስያዝ የሚያስችል ጭምር መሆኑን አንስተው÷ በሽፋን ስር ለሚደረጉ የምርመራ ሂደቶች ወይንም ልዩ የምርመራ ሂደቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ የሚከናወን መሆኑን ማስቀመጡን አብራርተዋል።
ይህም ፍርድ ቤቱ በመደበኛ የምርመራ ዘዴ ማስረጃ ማግኘት አዳጋች መሆኑን አምኖ በሰጠው ፈቃድና ትዕዛዝ መሠረት የሚከናወን መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ የምርመራ ዘዴ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚደረግ መረጃን ለማግኘት በጥብቅ ዲሲፕሊን እና በፍርድ ቤት ቁጥጥር ስር የሚከናወን ነው ብለዋል።
በአጠቃላይም የተሻሻለው አዋጅ የሀገርን ደህንነትና የህዝብን ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑን ነው አቶ ሙሉቀን ያብራሩት።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!