37 A+ በማምጣት የሁለት ዋንጫ ተሸላሚዋ ፈቲሃ አሕመድ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 359 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው ፈቲሃ አሕመድ የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
ተማሪ ፈቲሃ ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 37 A+ በማምጣት ነው በ4 ነጥብ የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ እና ከሴት ተመራቂዎች አሸናፊ የሆነችው፡፡
ሽልማቱ የልፋቴ ውጤትና የስኬቴ መጀመሪያ ነው የምትለው ተማሪ ፈቲሃ ፥ አላማን ለማሳካትና ከግብ ለመድረስ በትኩረት መስራት ይገባል ብላለች፡፡
በትምህርቷ ጠንክራ በመቀጠል ለሀገሯ የተሻለ አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደምትሰራም ነው የተናገረችው።
ተማሪ ፈቲሃ ለስኬት እንድትበቃ እገዛ ላደረጉ መምህራን እና ቤተሰቦቿ ምስጋና አቅርባለች።
በሰላም አሰፋ