Fana: At a Speed of Life!

5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ደማቁ እና አጓጊው 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምፃውያን ውድድር ከፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።

በውድድሩ የምድብ አንድ ሰባት ተወዳዳሪዎች ጴጥሮስ ማስረሻ፣ ግሩም ነብዩ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ ኤርሚያስ ዳኘው፣ ዮሴፍ ጉልላት፣ ኤፍሬም ጌታቸው እና ማዕረግ ኃይሉ በሦስተኛ ሳምንት ውድድራቸው በቀጥታ ስርጭት ይፎካከራሉ።

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው የፋና ላምሮት ድምጻውያን ውድድር ላይ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል።

በዕለቱ አንድ አንጋፋ እና ተወዳጅ ሙዚቀኛ በክብር እንግድነት ይገኛል።

ውድድሩ በፋና ቴሌቪዥን እና በሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎች ለሚሳተፉበት የ13ኛው ሳምንት የፍፃሜ ውድድር ለማለፍ ይወዳደራሉ።

ለአሸናፊዎች ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን÷ የዋንጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማትም ይጠብቃቸዋል።

በለምለም ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.