Fana: At a Speed of Life!

ኢንተርፖል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር ይሰራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (ኢንተርፖል) ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር እሰራለሁ አለ።

የአፍሪካ ህብረት  ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ከኢንተርፖል ፕሬዚዳንት አህመድ ናስር አል ራይዚ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የህብረቱ ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ፤ ኢንተርፖል ህግን በማስከበር እና ዓለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነትን በመጠበቅ ረገድ የሚያደርገውን ትብብር አድንቀዋል፡፡

ኢንተርፖል በአፍሪካ ህብረት ስር ለሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የፖሊስ ትብብር (አፍሪፖል) እያደረገ ላለው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አህመድ ናስር አል ራይዚ በበኩላቸው÷ ተቋማቸው ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በቀጣይም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመዋጋት እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ኢንተርፖል ከአፍሪካ ህብረት ጋር መስራቱን እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.