Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ563 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ ይለማል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017/18 የመኸር ወቅት በተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ ከ563 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው።

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ በመኸር ወቅት ከሚለማው መሬት ከ54 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።

በአዝዕርት ሰብሎች 421 ሺህ 430 ሄክታር መሬት ለማልማትና 12 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በአትክልትና ስራስር ሰብሎች 68 ሺህ 148 ሄክታር በማልማት 16 ሚሊየን 644 ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል።

እንዲሁም በፍራፍሬ ሰብሎች 27 ሺህ 664 ሄክታር መሬት በማልማት 8 ሚሊየን 857 ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በቋሚ ሰብሎች 73 ሺህ 752 ሄክታር በማልማት 26 ሚሊየን 121 ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይም በዘንድሮው የመኸር አዝመራ በሁሉም አካባቢ ምርታማነትን ማመጣጠን ላይ በትኩረት ይሰራልም ነው ያሉት።

እቅዱን ለማሳካት ከግንቦት 16 ጀምሮ ከክልል ከፍተኛ አመራር እስከ ማህበረሰብ የዘለቀ ተሳትፏዊ የመኸር ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄ ተካሂዶ ወደ ተግባር መገባቱንም አስታውሰዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.