ማርቲን ዙባሜንዲ አርሰናልን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ማርቲን ዙቢሜንዲ በይፋ መድፈኞቹን ተቀላቅሏል።
የ26 ዓመቱ ዙቢሜንዲ በ60 ሚሊየን ፓውንድ ነው ከስፔኑ ሪያል ሶሴዳድ የሰሜን ለንደኑን ክለብ የተቀላቀለው፡፡
በሪያል ሶሴዳድ ቤት ጠንካራ አቋሙን ማሳየት የቻለው ዙቢሜንዲ ለክለቡ በሁሉም ጨዋታዎች 236 ጊዜ ተሰልፎ ተጫውቷል።
ዙቢሜንዲ በቀጣዩ የውድድር ዓመት አርሰናልን የመሐል ክፍል ያጠናክራል የተባለ ሲሆን፤ ከሌላኛው የሀገሩ ልጅ ሚኬል ሜሬኖ ጋር ጠንካራ ጥምረት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡
ተጫዋቹ ወደ አርሰናል ያደረገው ዝውውር የእግር ኳስ ህይወቱ ትልቅ ውሳኔ መሆኑን ጠቅሶ፤ አርሰናልን እንደሚወድ እና የክለቡ የጨዋታ ስልት ምርጫው መሆኑን ተናግሯል፡፡