የብሪክስ ተፅዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል – ፕሬዚዳንት ፑቲን
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሪክስ በዓለም አቀፉ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ ያለው ተፅዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል አሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፡፡
17ኛው የብሪክስ ዓመታዊ ጉባኤ በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ በየነ መረብ መልክዕት ያስተላለፉት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ታዳጊ ሀገራትን ያሰባሰበው ብሪክስ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር አድጓል ብለዋል።
አባል ሀገራቱ የፈጠሩት ስትራቴጂካዊ ትብብር በዓለም አቀፉ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ በጎ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የዓለማችንን 40 በመቶ ኢኮኖሚ የሚሸፍኑት የብሪክስ አባላት በሀገራቸው ገንዘብ የሚያደርጉት የንግድ ልውውጥ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው፤ የሀገራቱን የካፒታል ኢንቨስትመንት የበለጠ ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት።
በተጨማሪም በግብርና ምርት ልውውጥ፣ በስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዘርፍ የአባል ሀገራቱ ትብብር እያደገ መምጣቱን አመላክተዋል፡፡
የባለብዙ ዋልታ ዓለምን ማረጋገጥ የብሪክስ በየነ መንግስታት ስብስብ ዋና ዓላማ መሆኑንም አስምረውበታል።
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!