Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጋር ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ምክር ቤት አባላት ጋር በእንጦጦ ተራራ ላይ ችግኝ ተክለዋል።

3ኛው የአዲስ አበባ ምክር ቤት 4ኛ አመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

የምክር ቤቱ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ ከመጀመሩ አስቀድሞ ‘በመትከል ማንሰራራት’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው 7ኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

በዚህም ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የምክር ቤቱ አባላት እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.