Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ሰራዊት 18 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በሰራዊቱ አባላት 18 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ አሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት የክረምት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ መምሪያ ዋና ግቢ ውስጥ ተጀምሯል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በወቅቱ እንዳሉት፤ ሰራዊቱ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል።

ዘንድሮም ከዛሬ ጀምሮ ሰራዊቱ በያለበት የግዳጅ ቀጣና የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ያከናውናል ነው ያሉት።

በመከላከያ ሰራዊት 18 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ አንስተው÷ “ከካምፓችን ወደ ሕዝባችን” በሚል መሪ ሃሳብ የበጎ ፍቃድ ስራዎች እንደሚከናወኑም ተናግረዋል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር አመራሮች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.