Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል አሉ፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶችን መርቀን ለአገልግልሎት ክፍት አድርገናል ብለዋል።

ከፕሮጀክቶቹ መካከል 14 አዳዲስ ትምህርትቤቶች፣ 64 ማስፋፊያ የተደረገባቸው ነባር ትምህርት ቤቶች፣ 1 ሺህ 655 የመማሪያ ክፍሎች እንዲሁም የአይሲቲ ክፍሎች እና ቤተ ሙከራዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መጽሐፍት፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎት  ጨምሮ ትምህርት ቤቶችን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና ለመምህራን ምቹ የማድረግ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ትውልድን ለማነጽ በተሰራው ሥራ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ከንቲባዋ ምስጋና ማቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.