በለንደን ዳይመንድ ሊግ የ1 ማይል ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በለንደን ዳይመንድ ሊግ የ1 ማይል ሴቶች ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የቦታውን ክበረወሰን በማሻሻል አሸነፈች፡፡
ጉዳፍ ርቀቱን በ4 ደቂቃ ከ11 ሰኮንድ ከ88 ማይክሮ ሰኮንድ በመግባት ነው ያሸነፈችው፡፡
ጉዳፍ የገባችበት ሰዓት የርቀቱ የምንጊዜም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ሲመዘገብ የቦታው ደግሞ ክበረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡