Fana: At a Speed of Life!

ራሽፎርድ ባርሴሎናን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ውል ከማንቼስተር ዩናይትድ አስፈርሟል፡፡

በዚህ መሰረትም ማርከስ ራሽፎርድ ለአንድ የውድድር ዓመት በውሰት ውል በባርሴሎና ቆይታ ይኖረዋል፡፡

ባርሴሎና በውሰት ውሉ ላይ የተቀመጠውን የመግዛት አማራጭ በመጠቀም ራሽፎርድን በቋሚነት ማስፈረም ይችላል፡፡

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ራሽፎርድ በባርሴሎና በሚኖረው ቆይታ 14 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስም ተረጋግጧል፡፡

የ27 ዓመቱ ተጫዋች በ2024/25 የውድድር ዓመት ከጥር ወር ጀምሮ እስከ ውድደር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በውሰት ውል በአስቶንቪላ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ማርከስ ራሽፎርድ ባርሴሎናን መቀላቀሉን ተከትሎ ማንቼስተር ዩናይትድ በማህበራዊ ትስስር ገፁ መልካም ምኞቱን ገልጾለታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.