Fana: At a Speed of Life!

አርሰናል ክሪስቲያን ሞስኬራን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል ወጣቱን ስፔናዊ ተከላካይ ክሪስቲያን ሞስኬራ ከቫሌንሲያ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ለ21 ዓመቱ ተጫዋች 13 ሚሊየን ፓውንድ መነሻ የዝውውር ሂሳብ ይከፍላል፡፡

ክሪስቲያን ሞስኬራ በመድፈኞቹ ቤት ለአምስት ዓመት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን፥ አርሰናል ተጫዋቹን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማቆየት የሚችልበት ማራጭ በውሉ ተካቷል፡፡

አርሰናል በተመሳሳይ ቪክተር ጎከሬሽን ከስፖርቲንግ ሊዝበን ለማስፈረም መስማማቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.