Fana: At a Speed of Life!

ሆስፒታሉ ወደ ቀደመ አቅሙ ተመልሶ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአጭር ጊዜ ወደ ቀደመ አቅሙ ተመልሶ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል እየተሰራ ነው አሉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው ዕለት በቅርቡ የእሳት አደጋ ያጋጠመውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው በሆስፒታሉ ተከስቶ የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።

በዚህም በክልሉ አንጋፋ በሆነው ሆስፒታል ላይ የተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን በመመልከት÷ በደረሰው ጉዳት ዙሪያ ከሆስፒታሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በወይይቱም ወቅት ሆስፒታሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀደመ ተቋማዊ አቅሙ ተመልሶ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አንስተው÷ የክልሉን ሕዝብ የተለመደ ሕብረትና ትብብር በተጨባጭ የሚያሳይ ሀብት የማሰባሰብ ስራ እንደሚከናወን አብራርተዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ የክልሉ መንግስት ለሆስፒታሉ መልሶ ግንባታ 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደረግ ገልጸው÷ በክልሉ የሚገኙ 12 ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮችም ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ለሆስፒታሉ የጋሞ ዞን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር 1 ሚሊየን ብር እንዲሁም የጎፋ ዞን አስተዳደር 658 ሺህ ብር የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውም ተገልጿል።

በማቱሳላ ማቴዎስ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook WMCC

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.