Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በአንድ ጀንበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል በነገው ዕለት በአንድ ጀንበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ አለ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ።

ቢሮው ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ እንደገለጸው÷ በነገው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅድ ለማሳካት በአፋር ክልል አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።

የአፋር ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 10 ነጥብ 25 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን የገለጸው ቢሮው÷ በአንድ ጀንበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉንም አስታውቋል።

በነገው ዕለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በተገኙበት የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ዘመቻ እንደሚካሄድም አመልክቷል።

ከሚተከሉት 60 በመቶ የሚሆኑ ችግኞች ለምግብነት እንደሚውሉና 40 በመቶው ደግሞ ለጥላና ለደን ልማት የሚውሉ መሆናቸውንም ጠቁሟል።

የተከላ መርሐ ግብሩ በ5 ሺህ 466 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚከናወንና ከ510 ሺህ በላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.