የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው የኢትዮያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቷል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከብሮድካስት እና ስም ስያሜ መብት የሚያገኙት ክፍፍል ይፋ አድርጓል።
በዚህም ዓመቱን በአሸናፊነት ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን 40 ሚሊየን 295 ሺህ ብር በላይ ማግኘቱ ተገልጿል።
እንዲሁም በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና 37 ሚሊየን 703 ሺህ ብር ያገኘ ሌላኛው ክለብ እንደሆነ ተመላክቷል።
በተጨማሪም ባሕር ዳር ከተማ 35 ሚሊየን 281 ሺህ 37 ብር ማግኘቱን ያመላከተው አክሲዮን ማህበሩ÷ በአጠቃላይ በ2017 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ለሆኑ ክለቦች 428 ሚሊየን 846 ሺህ ብር ማከፋፈሉን ነው ያስታወቀው።
በሰለሞን በቀለ