ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በነገው ዕለት በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገብተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ የውብ ባህል ባለቤት፣ የአብሮነትና የሰላም ማዕከል፣ የምስራቋ ብርሃን፣ የአያሌ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት እና የለም መሬት መገኛ በሆነው የሶማሌ ክልል ርዕሰ ከተማ ነፋሻማዋ ጅግጅጋ ከተማ ገብተናል ብለዋል።፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ካቢኔያቸው እና የጅግጅጋ ከተማ ህዝብ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።
በቆይታቸውም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችና የኮሪደር ልማት የስራ ሂደትን እንደሚመለከቱ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ታሪካዊውን “በመትከል ማንሰራራት” በ7ኛ ዓመት 700 ሚሊየን ችግኞች በአንድ ጀምበር ከሀገር ወዳዱ የሶማሌ ክልል ህዝብ ጋር አብረን የምንከውን ይሆናል ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!