የአካባቢ ጥበቃ ስራ ውጤቱ በሂደት እየተገለጠ የሚሄድ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል አለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮች የሚተከሉ ችግኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታውሰዋል።
በዚህም በአንድ ጀንበር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ የመትከል ዘመቻ ከተጀመረ 5 ዓመታት ማስቆጠሩን አንስተው÷ በነገው ዕለትም 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ለዕቅዱ መሳካት ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው መዋቅር ከየአካባቢው አየር ሁኔታ ጋር ምቹ የሆኑ ችግኞችን የመለየት እና ማዘጋጀት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
እንዲሁም የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ተቆፍረው መዘጋጀታቸውን እና በነገው ዕለት በሚደረገው የችግኝ ተከላ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው አሻራቸውን እንዲያኖሩ አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።
የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ ውጤቱ በሂደት እየተገለጠ የሚሄድ እንደሆነ እና ባለፉት 7 ዓመታት በተካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውንም አብራርተዋል።
አካባቢ ሲጠበቅ ከሚሰጣቸው ጥቅሞች መካከል ምርታማነትን ማሳደግ፣ የአፈር ለምነትን መጨመር፣ የተሻለ የዝናብ ፍሰት እንዲኖር ማድረግና የግብርና ምርታማነት መጨመርን ለአብነት አንስተዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ቡና፣ መኖ እና ሌሎች በርካታ ጥቅሞችን በሚያስገኙ ችግኞች ላይ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ በዚህም ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ለበርካቶች የስራ ዕድል እየፈጠረ እንደሆነና ለሌማት ትሩፋት እና ሌሎች ኢኒሼቲቮች አጋዥ በመሆን በምግብ ራሳችንን የመቻል ጥረታችንን በከፍተኛ ደረጃ ያግዛልም ነው ያሉት።
የዘንድሮ “በመትከትል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ሲታቀድ በዋናነት ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በባለቤትነት ስሜት እና በቁርጠኝነት እንደሚረባረብ እምነት በመጣል እንደሆነም ተናግረዋል።
በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነቂስ ወጥቶ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ አቶ ተስፋሁን ጥሪ አቅርበዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!