Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው – ቢልለኔ ስዩም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለታዳሽ ሃይል መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል አሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም፡፡

ቢልለኔ ስዩም ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እቅድ እንዲሳካ ዜጎችን እያነቃቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መርሐ ግብሩን በጅማ በጠዋት ካስጀመሩ በኋላ አዲስ አበባ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አመራሮች እና ከሪፐብሊካን ጋርድ አባላት ጋር በየካ ተራራ ችግኝ መትከላቸውን አንስተዋል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ የፍራፍሬና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ጠቁመው ÷ ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ለቡና ልማት፣ ለታዳሽ ሃይል መስፋፋት፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች እንዳሉት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአረንጓዴ ዐሻራ ትርጉም ችግኝ ከመትከል በላይ መሆኑን በመገንዘብ በመርሐ ግብሩ በንቃት እንዲሳተፍ ጠይቀዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.