ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ሕብረተሰብ ለአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ ስኬት ላሳየው ተነሳሽነት አመሰገኑ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአንድ ጀንበር የ700 ሚሊየን ችግኝ ተከላን ለማሳካት ዐሻራ የማኖር ጉዞ ከዕቅድ በላይ ተሳክቷል አሉ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በስኬት የተጠናቀቀውን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም የአንድ ጀንበር የ700 ሚሊየን ችግኝ ተከላን ለማሳካት ዐሻራ የማኖር ጉዟችንን ከዕቅድ በላይ አሳክተናል ብለዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሃሰን የበሬ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻሊይዝድ ሆስፒታል ችግኝ መትከላቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ሁሉም ሕብረተሰብ ሀገራዊ ግቡን ለማሳካት ከማለዳው ጀምሮ ችግኝ ለመትከል ላሳየው ተነሳሽነትም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡