ቶማስ ሙለር ቫንኩቨርን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጀርመናዊው ተጫዋች ቶማስ ሙለር ወደ ካናዳ በማቅናት ቫንኩቨርን በይፋ ተቀላቅሏል።
የ35 ዓመቱ ሙለር ከበርካታ ዓመታት የባየርን ሙኒክ ቆይታ በኃላ ከጀርመኑ ክለብ ጋር በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት መለያየቱ ይታወሳል።
ሙለር በጀርመኑ ክለብ ባየርን ሙኒክ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
ተጫዋቹ በሙኒክ ለመቆየት ውሉን ለማራዘም ፈቃደኛ የነበረ ቢሆንም ክለቡ ባለመፈለጉ መለያየታቸው አይዘነጋም።
ጀርመናዊው የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ቶማስ ሙለር በቫንኩቨር ቆይታው 13 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ተረጋግጧል።
የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ክለብ የሆነው ሲንሲናቲ ከዚህ በፊት ለቶማስ ሙለር የዝውውር ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ መዳረሻው ቫንኩቨር ሆኗል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ