Fana: At a Speed of Life!

ኦስማን ዴምቤሌ እና ላሚን ያማል ለባሎንዶር አሸናፊነት ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፒኤስጂው ኦስማን ዴምቤሌ እና የባርሴሎናው ላሚን ያማል ለባሎንዶር አሸናፊነት ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የ2025 የባሎንዶር፣ ኮፓ፣ ያሲን እና የአሰልጣኞች ሽልማት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በፈረንጆቹ መስከረም ወር በፓሪስ በሚካሄደው የ2025 የባሎንዶር እጩዎች ዝርዝር ይፋ ሲደረግ ኦስማን ዴምቤሌ፣ ላሚን ያማል እና ሞሐመድ ሳላህ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

ጁድ ቤሊንግሀም፣ ዴንዚል ዱምፍሪስ፣ ሰርሁ ጉራሲ፣ ሀላንድ፣ ዮኮሬሽ፣ ሃሪ ኬን፣ አሽራፍ ሃኪሚ፣ ክቫራትክሄሊያ፣ ሌዋንዶውስኪ፣ ማክአሊስተር፣ ላውታሮ ማርቲኔዝ፣ ኑኖ ሜንዴስ፣ ዦአዎ ኔቬሽ፣ ፔድሪ፣ ማይክል ኦሊሴ፣ ራፊንሃ፣ ዲክላን ራይስ፣ ቫንዳይክ፣ ፋቢያን ሩይዝ፣ ቪኒሺየስ ጁኒየር፣ ፍሎሪያን ቪርትስ እና ቪቲንሃ ከ30ዎቹ እጩዎች ውስጥ ተካትተዋል፡፡

በ21 ዓመት በታች (ኮፓ ትሮፊ) እጩዎች ደግሞ፡- ፓው ኩባርሲ፣ አዩብ ቡአዲ፣ ደሲር ዱዌ፣ ኢስቴቫዎ ዊሊያን፣ ዲን ሁይሰን፣ ማይልስ ሌዊስ-ስኬሊ፣ ሮድሪጎ ሞራ፣ ዦአዎ ኔቬሽ፣ ላሚን ያማል፣ ኬናን ይልዲዝ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

አሊሰን ቤከር፣ ያሲኔ ቦኖ፣ሉካስ ቼቫሊየር፣ ቲቦ ኮርቱዋ፣ ጂያንሉጂ ዶናሩማ፣ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ፣ ጃን ኦብላክ፣ ዴቪድ ራያ፣ ማትዝ ሴልስ ያን ሶመር በምርጥ ግብ ጠባቂ (ያሲን ትሮፊ) በእጩነት የቀረቡ ግብ ጠባቂዎች ናቸው፡፡

የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ደግሞ:- አንቶኒዮ ኮንቴ፣ ሉዊስ ኤንሪኬ፣ ሃንሲ ፍሊክ፣ ኤንዞ ማሬስካ እና አርኔ ስሎት ሆነዋል፡፡

ባርሴሎና፣ ቦታፎጎ፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል እና ፒኤስጂ የአመቱ ምርጥ ክለብ እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.