Fana: At a Speed of Life!

በድባጤ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው ከድባጤ ወደ ገሰሰ ቀበሌ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው የደረሰው።

በተከሰተው አደጋም የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ብርሃኑ እጄታ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ጠቁመው፥ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክተዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝም ነው ኮማንደር ብርሃኑ የገለጹት።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.