83 በመቶ አገልግሎቶቹን በኦንላይን የሰጠው ተቋም…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አሰራሩን በማዘመን 83 በመቶ አገልግሎቶቹን በኦንላይን እየሰጠ ነው፡፡
የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ እቱገላ ተሾማ እንዳሉት ÷ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት በቴክኖሎጂ የታገዝ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ተሰርቷል፡፡
በዚህም 986 ሺህ 614 ጉዳዮችን ለማስተናገድ ታቀዶ 946 ሺህ 908 ጉዳዮችን አረጋግጦ መመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ፋይዳ መታወቂያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው ያስረዱት፡፡
ከተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንም ሥራ አስፈጻሚዋ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የተስተናገዱ ሲሆን ÷ ልዩ ችግር ላለባቸው 16 ሺህ 717 ዜጎች ደግሞ ባሉበት ቦታ አግልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡
ተቋሙ 787 ሺህ 896 አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠቱን ጠቁመው ÷ በዚህም 83 በመቶ አገልግሎቶችን በኦንላይን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
271 ሐሰተኛ ነዶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጋቸውን የተናገሩት ሥራ አስፈጻሚዋ ÷ ለዚህም የፋይዳ መታወቂያ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!