Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና አለው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል መታወቂያ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና አለው አለ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም።

“የኢትዮጵያ ሴቶች ከየት ወዴት” በሚል ሃሳብ የለውጡ ትሩፋት የሆኑ ሴት አመራሮች መድረክ ላይ የፕሮግራሙ የሕግና ፖሊሲ ክፍል ኃላፊ ገብሬላ አብርሃም “ሴቶችና ብሄራዊ መታወቂያ” በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ያለ ሴቶች ተሳትፎ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ኃላፊዋ በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

በለውጡ ዓመታት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዲጂታል መታወቂያ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገትና የተሳለጠ አገልግሎት አሰጣጥ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም አንስተዋል።

ዲጂታል መታወቂያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን በመግለጽ በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ገቢራዊ ከተደረገ በኋላ አገልግሎት አሰጣጡን ግልጽና ቀልጣፋ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ21 ሚሊየን በላይ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸውንና ከተመዘገቡት መካከል 40 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ የሴቶችን የተሳትፎ ከዚህም በላይ ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ለሴቶች ሕጋዊ ዋስትና የሚሰጥ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፏቸውን ለማጎልበት ሚናው የጎላ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ሴት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሴቶች በዲጂታል መታወቂያ ላይ በቂ መረጃ ኖሯቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር አለባቸው ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.