Fana: At a Speed of Life!

ሪያል ማድሪድ ፍራንኮ ማስታንቱኖን በይፋ አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሪያል ማድሪድ አርጀንቲናዊውን ተጫዋች ፍራንኮ ማስታንቱኖ ከሪቨር ፕሌት ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

የስፔኑ ክለብ ለአርጀንቲናዊው አማካይ ዝውውር 45 ሚሊየን ዩሮ ወጪ አድርጓል፡፡

የ18 ዓመቱ ተጫዋች በልደቱ ቀን ለስድስት ዓመታት በሳንቲያጎ በርናባው የሚያቆየውን ውል ፈርሟል፡፡

ማስታንቱኖ በዚሁ ወቅት፥ የዓለማችን ትልቁን ክለብ ሪያል ማድሪድን በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ፥ ህልሜን እየኖርኩ ነው ሲል ተደምጧል፡፡

ተጫዋቹ በሪያል ማድሪድ በሚኖረው ቆይታ 30 ቁጥር ማልያን እንደሚለብስ ተረጋግጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.