Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫ ነገ ይጀመራል አለ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ።
የምርጫ አሥፈጻሚ ቦርዱ ሰብሳቢ አብዱላዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ÷ ለሀገር አቀፍ መጅሊስ ምርጫ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች የቅድመ ምርጫ ሥራዎች ተጠናቅቀዋል፡፡
አሁን ላይ የምርጫ ዝግጅት ምዕራፉን በማጠናቀቅ ወደ ምርጫ መሸጋገሩንም አመልክተዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ምርጫው ከነገ ነሐሴ 9 ጀምሮ እስከ እሑድ ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ነው የገለጹት፡፡
በነገው ዕለት የዑለማዎች ምርጫ የሚከናወን ሲሆን÷ በቀጣይ ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሠራተኛውን ማሕበረሰብ ለሚወክሉ ተመራጮች ድምጽ ይሰጣል ብለዋል፡፡
ምርጫውን አሳታፊ፣ አካታችና ፍትሃዊ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን ጠቁመው ÷ ለምርጫው ከ13 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ለቀጣይ 5 ዓመታት ይወክለኛል የሚለውን ወኪል ካርድ ባወጣባቸው መስጅዶች በመገኘት ድምጽ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጀማል አሕመድ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.