በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 5 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡
ትናንት የተጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲካሄዱ ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ አስቶን ቪላ ከኒውካስል ጋር ይገናኛል።
እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዓመት በሊጉ ደካማ እንቅስቃሴ የነበረው ቶተንሃም 11 ሰዓት ላይ ዘንደሮ ወደ ሊጉ ካደገው በርንለይ ጋር ሲገናኙ÷ ብራይተን ከፉልሃም፣ ሰንደርላንድ ከዌስትሃም በተመሳሳይ ሰዓት ይጫወታሉ።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ወልቭስ ከፔፕ ጓርዲዎላው ማንቼስተር ሲቲ ጋር የሚያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በትናንትናው ዕለት በተጀመረው የሊጉ መጀመሪያ ጨዋታ ሊቨርፑል በርንማውዝን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በዮናስ ጌትነት