Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ ይገባል አሉ፡፡
የዲጂታል አማራ ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ቴክኖሎጂን መጠቀም የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን መሰረታዊ ግዴታ እየሆነ መጥቷል፡፡
ዲጂታል አማራ ኢኒሺዬቲቭ ክልሉ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የያዛቸውን ግቦች ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።
የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ ቴክኖሎጂ መር ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለመሆንና ፈጣንና ተአማኒነት ያላቸው መረጃዎችን ለመለዋወጥ ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ቴክኖሎጂን አውቆ መጠቀም፣ መፍጠርና የሥራ ዕድል መጠቀሚያ የሚያደርግ ትውልድ መገንባት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
ዲጂታል አማራ ኢኒሺዬቲቩ ከ2018 እስከ 2022 ዓ.ም በክልሉ 5 ሚሊየን ዜጎችን በማሰልጠን የ21ኛው ክፍለ ዘመን የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
ቴክኖሎጂው ተማሪዎች ትምህርታቸውን በኦንላይንና ኦፍላይን የሚማሩበትን ሥርዓት ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በደሳለኝ ቢራራ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.