Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ሶስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ሊጉን በሽንፈት የጀመሩት ማንቼስተር ዩናይትዶች የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል እያለሙ ዛሬ ምሽት 12:30 ላይ በክራቨን ኮቴጅ ፉልሃምን ይገጥማሉ።

በአርሰናል ሽንፈት ባስተናገዱበት ጨዋታ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያስመለከቱት ዩናይትዶች በዛሬው ጨዋታ ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት አግኝተዋል።

በሌሎች የእለቱ መርሐ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ ከኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ኤቨርተን ከብራይተን ቀን 10 ሰዓት ይጫወታሉ።

ትናንት በተካሄደው የሊጉ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ዮከሬሽ (2)፣ ዩሪየን ቲምበር (2) እና ቡካዮ ሳካ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሊድስ ዩናይትድን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቦርንማውዝ ወልቭስን፣ ብሬንትፎርድ አስቶን ቪላን በተመሳሳይ 1 ለ 0 እንዲሁም በርንሌይ ሰንደርላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል፡፡

በመጀመሪያው ሳምንት ከሜዳው ውጪ ድል ቀንቶት የነበረው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ቶተንሃምን አስተናግዶ 2 ለ 0 ተሸንፏል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.