Fana: At a Speed of Life!

ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ከፈተች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከፍታለች፡፡

የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው የኮሎሚቢያ ኤምባሲን በአዲስ አበባ መርቀው ከፍተዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ የኢትዮጵያና ኮሎምቢያን ግንኙነት ለማጠናከር ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

ኮሎምቢያ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ መክፈቷ የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኮሎምቢያ ጋር ያላትን ግንኙነት ብራዚል በሚገኘው ኤምባሲዋ አማካኝነት የምታስፈጽም መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.